untitled
viviti




በእውነት የ14ኛውን የዓለም ዋንጫ ብራዚልና ስዊድን ሲጫወቱ ለማየት አስቤያለሁ፡፡ የእግር ኳስ ስሜቴ ብዙም አይገፍኝ፡፡ እንዲያው በኳስ አርዕስት ጓደኞቼ ሲያወሩ የበይ ተመልካች ዓይነት እንዳልሆን ብዬ ነው፡፡ ሰዓቴን መልከት ሳረግ አንድ ሰዓት ከሩብ ትላላች፡፡ የእሁድ ማታ አንድ ሰዓት ከሩብ በአሰላ ከተማ፡፡ ለምን ሲኒማ አልገባም በማለት ቲኬት ቆርጬ ዘው አልኩ፡፡ ፊልሙ የቻይና ካራቴ ኩምክና ስነ ነበር እልፎ አልፎ ፈገግ እያደረገኝ ምስራቅ ትዝ እለችኝ፡፡ ዛሬ ማታ 12 ሰዓት አካበባቢ አግኝቻት ሰላም ተባብለን ዛሬን እንኳን እንድትቆይ ሰጋባባት ነገ ሥራ መግባት አለብኝ ብላ ድርቅ አለች፡፡ ሥር ከገባች ያገኝኋት ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ነበረ የምስራች አልኳት ምስር ብላ በማለት እንደገና ተሳሳምን፡፡ ሠራተኛም ስለሆንሽ የምስራቹን እናክብራው ብዬ ሃሳብ ባቀርብም የማይሆን ሆነ፡፡
ምስራቅ የቀይ ዳማ የምትባል፣ ቀመቷ ዘለግና ፈርጠም ያለ፣ ፈገግ ስትል በውሃ የበለዙ ጥርሶቿ ገሃድ፣ ቢወጡም ውበቷን የማያጠፋበት ጎበል ነች፡፡ ከተዋወቅን አንድ ዓመት ቢያልፈንም ያለንበት የመኖሪያ ርቀት እንደልባችን ተገናኝተን እንድንጫወት አላስቻለንም፡፡ በተገናኝንባቸው ሰዓታት ግን የልብ ለልብ የተግባባን ሆነናል፡፡ ወሬ አጥተን ሳንደባበር 4 ሰዓት 5 ሰዓት ተጫውተናል፡፡ ያለችበት ከተማ ስሄድም ሆቴል አሲዛኝ ስንጫወት አምሽተን ወደ ቤት ሸኝጫት ከመመለስ በቀር በፍቅር ጉዳይ ገና ነን፡፡ ቢሆንም መንፈሱ እንዳለ ሁለታችንም እናውቀዋለን፡፡ እንዲያው በደፈናው በጣም ጥሩ ጓደኛሞች ለመባል ችለናል፡፡ ዛሬ ታዲያ በአጋጣሚ ነበር እሷማ ጓደኛዋ ዘመዶች ጋር ከጓደኛዋ ጋር መጥታ፣ እኔም የሦስት ቀን ፈቃዴን ጫረሼ ወደ ምሠራበት ቦታ ለመሄድ መንገድ ሳድር የተገናኝ ነው፡፡ ዛሬን እደሪ እቤት ደውለሽ ብላትም የስራውን ሁኔታ ጠቅላ አልበነር ያለቸውና ወደና ሁን ጎደኛህን ሰላም በልልኝ ብላ የተሰናበተቸኝ፡፡
ፊልሙ ሲያበቃ ነው እኔም ከሃሳቤ የባነንኩት፡፡ ሆዴንም ስለሞረሞረኝ የምግብ ፍላጎትም ባይኖረኝ ቀማምሼ ቴሌቪዥን ለመከታተል ጎራ አልኩ፡፡ ባጋጣሚ የቴሌቪዥን የሰሞኑ ተመልካቸው ብዙ ስለ ነበር ክፍሏ ደግሞ ጠባብ ስለ ነበረች እንግዳ መቀበያው በር አካባቢ ወንበሮች ተደርድረዋል፡፡ ቴሌቪዥኑ ከቡና ቤቱ በር ላይ ደረጃው ሥር ከፍ ያለ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጧል፡፡ እንዳንድ ተመልካቶች ድምጽቸውን ዝጥ አርገው ይንሾካሾካሉ፡፡ የበረንዳው እንጨት አጠገብ አንድ ባዶአግዳሚ ስለ ነበር ሄጄ በመቀመጥ የእግር ኳስ ጨዋታውን መጠበበቅ ጀመርኩ፡፡ የሰሞኑን ጨዋታዎች በተመለከተ እንዳንድ ዜናዎች ይቀርቡ ነበር፡፡ የስፖርት ዜናው አልቆ በጣም የተጠበቀው የብረዚልና የስዊድን ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ዩናይትድ ስቴቴስ በቼከዝላቪኪያ 5 ለ 1፣ ሶብየጥ ህብረት በሩማኒያ 2 ለ0፣ መሸነፈቸው እዛ የተቀመጠውን ተመልካች ያነጋግረው ጀመር፡፡ ልክ 4፡00 ሠዓት ላይ ነበር/በኔ ሰዓት/ ዳኞች ወደ ሜዳው የገቡት፣ ተመልካቹንም ረጭ በላ ፀጥታ፣ ከቴሌቪዥኑም ኋላ ካለው ቡና ቤት እንዲት ገብል በመቅደም ጓደኛዋም ከኋላዋ በመከተል ወደ መኝታ ክፍሎች ሲያመሩ በዓይኔ በብረቱ የተመለከተኩት፡፡ ልጅቷ ምስራቅ ያልኳችሁ ለነገ ሥራ መድረስ ስለምፈልግ አላድርም ያለችኝ ናት፡፡ በዛው ደቂቃ ብዙ ነገሮች ተመላለሱብኝ፡፡ ካልም ዳውን የሚል የዶ/ር ፓልን መፍሐፍ ያነበብኩት በቅርብ ስለ ነበር ቁጣን ማስወገድ አይቻልም ማቀዝዝ እንጂ በሚለው ርዕስ ስር ንዴቱን ስላመጣው ነገር ረጋ ብሎ ማሰብ ይረዳል የሚለውን ሃሳብ አስታውሼ ውስጤ ግን እየጨሰና እየተኮማተረ አንድ ሌላ ብኩን ቤት አልኩ በሆዴ፡፡ ለነገሩ ግን ሸወደችኝ፡፡ በእውነት ሸወደችኝ፡፡

Web Hosting · Blog · Guestbooks · Message Forums · Mailing Lists
Easiest Website Builder ever! · Build your own toolbar · Free Talking Character · Email Marketing
powered by a free webtools company bravenet.com