አስፈሪው ሌሊት ሌሊቱ ረጭ ብሏል ምንም ኮሽጻ አይሰማም፡፡ እጄን ለማንቀሳቀሰ አንኳን አልደፍርም፡፡ ፀጥታውን ላለማደፍረሰ ፈርቼ፡፡ ከእንቅልፌ ምን እንደ ቀሰቀሰኝ አላውቅም ብቻ ነቅቻለሁ፡፡ በጀርባዬ እንደተጋለልኩ ጨለማውን ልክ እንደ ቆንጆ ገን አስፈሪ ሙዚቃ ማዳመጥ ጀመርኩ፡፡ ለትንሽ ጊዜ በኋላ በሩ ኳ ኳ ያለ መሰለኝ፡፡ አቤት ውስጥ ሌላ ሰው ቢኖር እንኳን እሱ ይሆናል የሚል መረጋገያ ይኖረኝ ነበር፡፡ ነገር ገን ብቻዬን ነኝ፡፡ ደንገጥ በማለት ተንፍሼን ወጥ አርጌ ያዝኩ፡፡ ቆየት ብሎ ደግሞ መስኮቱ ኳ ኳ ይላል፡፡ ሌባ በሩ በቀላሉ ስለማይከፈት መስኮቱን እየሞከረ ሳይሆን አልቀረም፡፡ እንዱያውም የኔ መስኮት ገፋጋፋ ሲደረግ ቶሎ የከፈታል፡፡ ይሄንን የሚያውቅ ውስጥ አዋቂ ሌባ ነው፡፡ በሩን የሚንኳኳውም እንደተኛሁ ለማረጋገጥ ይሆናል፡፡ ስለዚህ መበጨረሳን ልይ በማለት ካለሁበት አልተነቃነቅሁም፡፡ በተኛሁበት ሁኜም እስቲ አሁን ወንደላጤ ቤት ምን ይገኛል ብሎ ነው ያውም እኔ ቤት ያለችኝ ብርቄ ሬዲዮ ነች፡፡ በተረፈ የአዘቦ ቀን ልብስ ነው፡፡ ውስጥ አዋቂ ቢሆን ለአንድ ሬዲዮ ብሎ ሌሊት ቤት ሰብሮ አይገባምም፡ ከሩቅ አካባቢ የመጣ ይናልል፡ አያልኩ ሳስብ አንድ የሰማሁ ቀልድ ትዝ አለኝ፡፡
በከተማው አደጋኛ ዘራፊ ሰው አያገደለ የሚዘርፍ መጥቷል ተብሎ ተወርቷል፡፡ አንድ ባለሱቅ ነጋዴ ሱቁን ዘጋግቶ ሲያሸልብ የሱቁ መስኮት በመንኳኳት ይባንናል፡፡ ማን ነህ ብሎ ሲጠይቅ እኔ እከሌ ዘራፊው ነኝ ክፈት የሚል መልስ ያገኛልል፡ ይሄኔ ባለሱቁ የለሁም ሰብረህ ግባ! ብሎ መለሰለት አሉ፡፡ የኔ ነገር ቤቴን ሰርስሮ የሚገባ ሌላ ቤቴ ደጃፍ ላይ ሲንደፋደፍ የሰማሁን ቀልድ አስታውሳለሁ፡፡ የራሱ ሁኔታ ቢገርመኝም የመስቴ መንኳኳት ወድ አሁኑ መለሰኝ፡፡ እንዴ አረ ብዙ ናቸው መሰለኝ፡፡ ሹክሹክታ ነገር ይሰማኛል፡፡ ሸፍቶችስ ቢሆኑ መሳሪነገር ሳይዙ መቼም አይመጡ፡፡ ገን እኔ ቤት ምን ሲያደርጉ ይመጣሉ? እኔ ለራሴ አንድ ተራ ሠራተኛ ከሃብት ሃብት የለኝ፡፡ /ከንብረት ንብረት/ ከሥልጣን፡፡ አበው አይመጣምን ትተሸ ይመጣል አስሰቢ ይላሉ፡፡ ሲተርቱ ለማንኛውም ያቺን እንደ ዱላም እንደ ጩቤም የምታገለግለዋን የት አርጌያት ይሆን? አዎ የራስጌዬ ኮሞዲና ውስጥ፡፡ ቀስ ብዬ ከአልጋዬ ወርጄ ያችን ዱላ በመያዝ በባዶ እግሮቼ ጣቶች እየረገጥኩ ድምፅ ሰላሰማ የመኝታ ቤቴን በር ከፍቼ ሳሎን ገባሁ፡፡ እስካሁን ከመስኮቱ ጋር እየታገሉ ነው፡፡ ግድግዳ ሥር ጆሮዬን አስጠግቼ ሳዳምጥ ምንም ሹክሹክታ የለም፡፡ እንግዲህ ሌሎች ሄደዋል ማለት ነው ለብቻው ደሞ ከመስኮቱ ጋር የሚታገለው ደህና መሳሪ ስለያዘ በራሱ ተማምኖ ይሆናል፡፡ እሱም አንድ፣ እኔም አንድ፡፡ መትረየስ እንኳን ቢይዝ አይዝም እንጂ እኔ ቆንጆ ጬቤ አለኝ፡፡ አንገቱን ላይ እሸቀሸቅለታለሁሁ፡ እሱ መስኮቱን ከፍቶ ከገባ በኃለ መብራት አብርቶ መኝታ ከፍል ሰው ካ ድምፅ በማያሰማ ሹጉጥ ገድሎ ንብረት ዘርፈ ለመሄድ ነው የሚያስበው፡፡ ያውም እንቅል ጭልጭ እድርጎ የወሰደው ሰው ስለዚህ ይዘናጋል፡፡ እኔ ደግሞ ከቆንጆ እንቅልፍ ላይ የቀሰቀሰኝ ዘራፊ ሌባን መጨረሻውን በዓይኔ በመመስከር ለቅርስነት በተገባቸው ጩቤ ለኔ ባለድልነት መድቦታል፡፡ አድሉ ሳያደርግ አልቀረም፡፡ የሰማዩን ንጉስ ለተጠቂ አይደል የሚያዳላው፡፡
የመስኮቱ መንኳኳት እየበረታ መጣ፡፡ የቆምኩበት እግሬም ወለሉ ላይ የተነጠፈው ቅዝቃዜ እየተሰማኝ በሃሳቤ መቁነጥነጥ እበዛሁ፡፡ ፍርሃቴ እየጨመረ ሄደ፡፡ እስከዛሬ ድረስ ሰው ገድዬ አላውቅም፡፡ የገደል ሰው በህግ ፊት ይቆማል፡፡ ለኔስ ገድያ ስቅላት ይፈረድብ ይሆን? ሌባ ስለገደልኩ አያደርጉትም፡፡ ባይሆን ይሸልሙኛል፡፡ ከምድራችን ላይ አንድ የሰላም ህይወት ቀበኛ አጠፋሁ ማለት አይደል እንዴ? ግን ሌባው ጁዶ ቢችልስ? ይሄ መቼም ትልቅ አደጋ ነው፡፡ የጩቤውን ነገር ትቼ ብጮህ ይሻላል፡፡ የሰው ያለህ አረ ኡ በል ይሻላል፡፡ አይ ከዚህ ሌባ፣ ሌባ፣ ሌባ ያዙ ኡ … ማለት ይቀላል፡፡ ለምን ጎረቤቴን ጩቤዴን በጋሮ በኩል ተጠርቼ አልቀሰቅሰውም? ለዚህ ሁሉ አያፈጫሁ መብራቱን አብርቴ ጫማ ካደረኩ በኋላ ንፋስ እንደሚልግ ሰው በሩን ከፍቼ ወደ ወጪአልወጣም? ሌባውም ጋና መብራት ሲበራ ተነቃበኝ ብሎ እግሬ አውጬኝ ማለቱ አይቀርም፡፡ ከበፊቶቹ ዘዴዎች ሁሉ ይሄኛው ይመረጣል፡፡ ሎሎች ዘዴዎች በጎረቤቶቼ ያሳጡል፡፡ በሃሳቤ ካወጣሁ ካወረድኩ በኋላ በፍርሃት ለሣሎኑንም መብራት በግ አድርጌ ፍርሃቴን ለመሸፈን አያፋጨሁ በሩን ከፈት ሳደርግ ድምፅ በሌላው መሣሪያ የተወረወረ ነገር ለግንባሬ ታልሞ ዥው ብሎ ሲምዘገዘግ በድንጋጤ ጎንበስ ስል ከግድግዳው ጋር ተጋጭቶ መሬት ወደቀ፡፡ ድንጋጤው በረድ ሲል የተወረወረብኝን ነገር መልክት ሳደርገው አብድ የወረወረው ድንጋይ የሚያክል ጥቁር ጢንዚዛ ነበር፡፡
bravenet.com