untitled
viviti





ተመልካቶች ኡስስ …! ነገር በምሳሌ ያስተማሩን አበው ምስጋና ይድረሳቸውና ዝምታ ወርቅ ነው ይሉ ነበር፡፡ በምክንያት አውሮፓውያንም መቼ ዝም ማለት እንዳለበት የሚያውቅ ሰው ጅል አይደለም የሚል አባባል አላቸው፡፡ የአበውን ብሂል ሲያጠነክሩት፡፡ ለነገሩ አልኩ እንጂ ሃሳብን መግለጽ ከተፈለገ ዝምታም የሚገባው ካገኝ ይናገር የለ፡፡ ለዚህም ነበር ግርማ በጋሻው በቅጽ 2 ቁ 2 1980 መድረካችን እትም …ዝም ቃል… በሚል ርዕስ ሥር ‹… ያሸኝን ብላችሁ ያሰበኩትን ሁሉ፣ የዝምታው ዘዬ ባይሰማም ቃሉ፡፡ የሰሙ ሰምተዋል አውግተዋል ከኔ፣ በከንፈር እድምታ በሙት ምላሽ ቅኔ፡፡ ዝም ብዬ ዝም ብል ዝም ብሏል አትበሉ የዝምታው ዘዬ ሲጠፈቸው ውሎ፡፡ …› በማለት ያስፈሩት፡፡ ሺ ጉዜ ቢነግረውም የማይገባው እንዳለ ሁሉ ለማወቅ ለፈጠነ ግን ዝምታም ብዙ ይናገራል፡፡ ነገርን ነገር ያነሳዋል ሆኖ ነው እንጂ የጽሑፍ መነሻ በየአጋጣሚ የምሰማው ያለቦታቸው የሚነገሩ ንግግሮች ናቸው፡፡
እዚህም እዚያም የቼዝ ውድድር ይደረጋል፡፡ በየሁለት ተፎካካሪዎች መሐል፡፡ ተመልካቶችም ከሰው ይመለከታሉ፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ክንዳቸውን ጠረጴዛ ላይ ስደግፈው ግንባራቸውን እያሹ ያስባሉ፡፡ አልፎ አልፎ ሌባ ጣታቸውን ከንፈራቸው ላይ ጣል በማድረግ በየት ልሄድ በሚል ዓይነት ቅኝት የቼዝ /ሠንጠረዡን/ ይቃኛሉ፡፡ አስበውና ተጨንቀው ይሄዳሉ፡፡ በዚህን ጊዜ እንዳንዱ ተመልካች መቅበጥበጥ ይጀምራል፡፡ ጨዋታው ቀጥሎ ቅብጥብጡ ተመልካች ያስበውን ዓይነት መንገድ ተጫዋቹ ሲሄድ አዎን አየህ ገና ከቅደም የነበረው ዕድል ይሄው ነው፡፡ በሚቀጥለው አፈካሄድም ቼክ ኤንድ ቼዝ /ንጉሱና ንግስቲቷን በቁጥጥር ሥር/ ትለዋለህ፡፡ ወይም አየህ በዚህ አካሄድህ ንግስቲቷን ብታጣ መሸሸጊያ ገዳሙን አታጣውም ይለዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ተጫዋቹ ይሄኛውን አላየሁትም ነበር፡፡ ሲለው ሁለተኛው ተጫዋች ምን እንደ ሚሰማው መገመት አያስቸግርም፡፡ የቼክ ጨዋታ ግን እንኳን ከተመልካች ከባለጋራም ተጫዋች ንግግር የሚጠበቅበት አልነበረም፡፡ ስለዚህ ተመልካቶች እባካችሁ ፀጥታ! በሰው የተመላቸውም አረንጓዴዋ የካራምቡላ ስታዲየም ውስጥም የሚኖረው ጫጫታ እንኳን ተጫዋቹን ጊዜ ለማሳለፍ የመጣውንም የካራምቡላ አፍቃሪ ውጣና ብረር የሚያሰኝ ነው፡፡ የሚወቱት ማሰብ እስኪሳናቸው ድረስ በዚህ በኩል ብትሄድ ባሊናን /በካራምቡላው ጨዋታ ተፈላጊዋን ኳስ/ ታገኛታለህ፣ እኔ ብሆን አተራምሰው ነበር፣ በሜዛ ስፖንዳ /በግማሽ የመጫወቸው ወለል/ ቅረባት፣ ደርሶ መልስ ሂድ የማይሰጥ ምክር የለም ክፋቱ የሁሉም በአንድ ጊዜ ስሚወጣ ጫጫታው አያድርስ ነው ተጫዋቹ ኳሶቹ ባያንሱት እዛ ቆሞ እንዲህ አርግ፣ እንደዚያ አርግ በሚሉት አስተኳሾች /መካሪዎች/ እሱ ምንም ማሰብ እንደማይችል በነሱ ጭንቅላት የመመራ ሮቦት ማድረጋቸው ሲያቃጥለው ኳሱን እነሱ ከመከሩት አቅጣጫ በተቃራኒው ወርውሮ እምቢ ማለቱን በዝምታው ዘየው ይገለጻል፡፡ ዳሩ ማን የሚገባው ተገኝቶ ጭራሽ እንዲህ ብታደርገው ኖሮ ብው ኳስ ይዘው ወርውረው ሊያሳዩ የሚቃጡም አይጠፉም፡፡ /በሰው ሰዓት!/ የከተማው አካባቢ የካራምቡላ ጨዋታ በእረጋታና በፀጥታ የሚከናወን ሲሆን አልፎ አልፎ በጓደኛማች መካከል መረን ያልለቀቀ የቀልጆች ምልልስ ይሰማሉ፡፡ ምነዋ ታዲያ የኛ ካራምቡላ አፍቃሪዎች እንደማይሆን ሆኑ?
ፊልም እየታየ ነው፡፡ ብዙ ሰው ተቀምጦ ይከታተላል፡፡ ትንሽ ፈገግ የሚያደር፣ ወይ የሚያስቅ ነው ከተሰማ አምስት ደቂቃ ሙሉ ሆዱን ይዞ በሚያስገመግም ድምጽ ይሰቃል እንዳንዱ፡፡ ይሄኔ ተመልካች አጨብቦለት ከዛ ፊልሙም ብቀጥል ጥሩ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ፊልሙን ታሪ በእርካታ መከታተል እንዲቻል፡፡ ሌላው ደግሞ አለ፡፡ ፊልም ይእ የታየ ከጓደኛው ጋር የቤቱን ወግ የሚርቅ ነገር ግን ገንዘብና ጊዜውን ክፍሎ የመጣው ፊልም ለመመልከት ነው ሁኔታው መልኩን ቀይሮ አስር ደቂቃ ፊልሙን መከታተል ሳይችል ቀርቶ እንደገናም በአካባቢው የተቀመጡትንም ሰዎች ፀጥታ ነስቷቸው ይቆያል፡፡ ፊልም ለመመልከት የመጣ ሰው በፀጥታ ተከታትሎ እንዲሄድ ፊልም ቦታ የማውራት ልምድ ያላቸው ሰዎች ለፊልም ሠዓት እንኳን ቢታቀቡ የሞራል ግዴታቸውን እንደልምድ ያላቸው ሰዎች ለፊልም በሰዓት እንኳን ቢታቀቡ የሞል ግዴታቸውን እንደተወጡ ይቆራልና በየአጋጣሚው እባካቸሁ ሊባሊ ይገባል፡፡ ምሳ ከተባለ በኋላ ሻይ ቡና ሲባል የ6፡30 ዜና ይደመጣል፡፡ ከጉናችሁ ወንበር ሰላጣ የጠቀመጠ ወይ ግሩም ብሎ እዛው እብራችሁ የሰማችሁን ዜና ይደግምላችሁል፡፡ እሱ ያንሱ ዜና ሲደግምላችሁ ሌላ ዜና አልፋችኋል፡፡ ለነገሩ ዜና መደጋገሙ ስለማይቀር በማታው እዳምጠዋለሁ ብለው ይጽናናሉ ቢሆንም ግን ከጎናችሁ የተቀመጠውን ‹የማነው ችኮ› ማለታችሁ አይቀርም፡፡ በልባችሁ፡፡ እስካሁን ማለት የፈለኩት ሳይገባችሁ የቀረ አይስለኝም፡፡ ያላገባችሁ ካላችሁ ግን ዝም ብያለሁና በዝምታዬ ልተረዱኝ ሞክሩሩ፡

Web Hosting · Blog · Guestbooks · Message Forums · Mailing Lists
Easiest Website Builder ever! · Build your own toolbar · Free Talking Character · Email Marketing
powered by a free webtools company bravenet.com